Product Description
ብዙ ሰዎች “ተከተለኝ!” የሚለውን የጌታ ጥሪ ሰምተው መልስ ሰጥተዋል። ያለ እነርሱ ዛሬ ያለችን ቤት ክርስቲያን አትኖረንም ነበረ፤ ኢየሱስ ለእኛ ስላደረገው ሥራ የሚያበሥረውንም መልካም የምሥራች ቃል ወደ ጆሮአችን አይደርስም ነበረ። ኢየሱስን መከተሉ ቀላል ሆኖ ሳለ፣ ለምንድን ነው ታዲያ ሁኔታው ብዙ አማኞችን በጣም የሚፈትነው? ምክንያቱም ለየግል ሕይወታችንም ሆነ ለቤተክርስቲያን የሚሆነውን÷ በደቀ መዝሙርነት ውስጥ የተቋጠረውን በረከት መረዳት ባለመቻላችን ነው። ይህ የትምህርት መጽሐፍ የተጻፈውም በዚሁ ጒዳይ ላይ ለውጥ ለማምጣት ታስቦ ነው። መጽሐፉ በተናጠልም ሆነ በአስተማሪ በሚመራ አነስተኛ ቡድን ለሚካሄድ ትምህርት የሚውል ነው። ከሆነ ዘንድ፣ በሉ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንከተል!
ጸሐፊው ኤስኮ ሲሊያን የፊንላንድ ተወላጅ የሆኑና እ.ኤ.አ. 2017 ዓ·ም ከሄልሲንኪ ዩኒቨርስቲ በቅዱሳት መጻሕፍት ጥናት ዘርፍ የዶክትሬት ምሩቅ ናቸው። እ.ኤ.አ.1980 በፊንላንድ በምትገኝ ቤት ክርስቲያን ውስጥ በእረኝነት አገልግሎታቸውን ጀመሩ፤ አገልግሎቱም ለብዙ ዓመታት ቀጠለ። በኋላም እ.ኤ.አ. 1985 ከቤተሰባቸው ጋር ወደ እየሩሳሌም ተዛውረው ጡሮታ እስከወጡበት ጊዜ ድረስ ለ15 ዓመት ያህል በዚሁ ከተማ ኑረዋል። ከልጆቻቸው መካከል ሁለቱ የተወለዱትም በእየሩሳሌም ከተማ ነው። እ.ኤ.አ. 2003-2008 ሦስተኛ ዲግሪአቸው ለመማር በነበራቸው ዝግጅትም ኤስኮ በእየሩሳሌም በሚገኘው በኢቭሪት ዩኒቨርስቲ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱስንና የሴም ቋንቋዎችን በማጥናት ጊዜአቸውን አሳልፈዋል። እ.ኤ.አ. ከ2015 እስከ 2019 በኢየሩሳሌም ለመጨረሻ ጊዜ በቆየበት ወቅት በመጻፍ ተጠምዶበት የነበረው ይህ መጽሐፍ የተጻፈው የእስራኤሉን ብሉይ ኪዳን ወደ መሲሐዊ እምነት መርሆዎች በማቅረብ በዕለት ተዕለት ኑሮው ውስጥ ሊታገዝበት በማሰብ ነው።
Reviews
There are no reviews yet.